በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ መቋረጡን፣ መብራት ከዕረቡ ጀምሮ መጥፋቱን እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በዚህ ዘገባ ተካቷል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በዕረቡ ምሽት ዘገባችን ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ በመቋረጡ ምክንያት ችግር ውስጥ መኾናቸውን የገለጹት አምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ተማሪዎች በተጨማሪም መብራት እንደተቋረጠና ይህንንም ተከትሎ የግቢው ተማሪዎች በሙሉ ተቃውሞ ሲያቀርቡ አስለቃሽ ጭስ እንደተወረወረባቸውና እንደተደበደቡ አንዳንድ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።